የኢትዮ- ቴሌኮም የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ዛሬ የካቲት 21 2014 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በተገመገመበት ወቅት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የድርጅታቸው አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር 60 ነጥብ 8 ሚሊየን መድረሱን አስታውቀዋል፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ በክብርት ወ/ሮ ሰመሬታ ሰዋሰው የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ስር የሚገኙት የቡልቡላ እና የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝቷል፡፡
የገንዘብ ሚኒሰቴር ለሰራተኞቹ ልጆች ያዘጋጀውን ሕፃናት ማቆያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ አስመርቋል፡፡ የህፃናት ማቆያው ከ4 ወር- 3 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ልጆች አገልግሎት ይሰጣል፡፡
በገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ከሳውዲ አረቢያ የንጉስ ሰልማን የሰብአዊ እርዳታ ማእከል የበላይ ሀላፊ ከክቡር ዶ/ር አብዱላህ አልራቢሀ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ሰብአዊና የእርዳታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ ለተሰኘች ውብ ፕሮጀክት እውን መሆን በጋራ መቆም አንደሚገባውና ለልጆቻችን የተሸለች ኢትዮጵያን ማውረስ እንደሚጠበቅብን የገንዘብ ሚኒስቴር የፖሊሲ ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር እዮብ ተካለኝ ገለጹ፡፡
በ2014 በጀት አመት 2ኛ ሩብ ዓመት (ከጥቅምት-ታህሳስ) የ100 ቀን እቅድ አፈጻጸም በገንዘብ ሚኒስቴር በተገመገመበት ወቅት እንደተገለጸው በፌዴራል መንግስት ከሀገር ውስጥና ከልማት አጋሮች ለመሰብሰብ የታቀደውን የመንግስት ገቢ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ሲሆን፣ አፈጻጸሙም መልካም እንደነበር ተመልክቷል፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡
በጦርነትና በግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች መልሶ ማቋቋሚያ የሚውል የአምስት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መዘጋጀቱን የገንዘብ ሚኒስተር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ ገለጹ፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ለ30ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ “ሠላም ይስፈን በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም!” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የጸረ- ጾታዊ ጥቃት ቀን ዛሬ ኅዳር 29 2014 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒሰቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በጋራ ተከብሮ ውሏል፡፡
Copyright © 2025 MOF All Right Reserved